ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ጓንዡ ከተማ የመንገደኞች በረራ የጀመረበትን 20ኛ ዓመት አከበረ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ጓንዡ ከተማ የመንገደኞች በረራ የጀመረበትን 20ኛ ዓመት አክብሯል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የመንገደኞች በረራ የጀመረው ሕዳር 1996 ዓ.ም እንደነበር ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ ወደ ጓንዡ ከተማ በሣምንት 10 የመንገደኞች በረራ እያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

አየር መንገዱ በቻይና 10 የዕቃ ጭነት (ካርጎ) እና የመንገደኞች በረራ መዳረሻዎች እንዳሉትም ተገልጿል፡፡

በቅርቡ ወደ ቻይና በረራ የጀመረበትን 50ኛ ዓመት ማክበሩ ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም