ቀጥታ፡

አቶ ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ገቡ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2016(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ከሰዓት ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጁባ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀምስ ሞርጋን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በጁባ በሚኖራቸው ቆይታ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና ከሌሎችም የአገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክትም ለፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እንደሚሰጡ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም