በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደረገ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎችን የአገልግሎት ታሪፍ ማስተካከያ አደረገ፡፡
አዲሱ የታሪፍ ማስተካከያው ከነገ ጥቅምት 20 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው ቢሮው የገለጸው፡፡
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ቢሮው አዲስ ባሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ በጥብቅ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን በሚተላለፉት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
ይህ የታሪፍ ማስተካከያ የከተማ አውቶብስንና የቀላል ባቡርን የማይጨምር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ህብረተሰቡም ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥሙት፤ በአቅራብያው ለሚገኝ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያዎች እና ለትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም በአቅራቢያው ባለ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በአካልና በነፃ የስልክ መስመር 9417 ጥቆማ መስጠት የሚችል መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።