ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እና አየርላንድ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እና አየርላንድ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአየርላንድ የዓለም አቀፍ ልማትና ዳያስፖራ ሚኒስትር ዴኤታ ሲያን ፊሊሚንግን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና አየርላንድ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በበርካታ የትብብር ማዕቀፎች እንድታሳድግ አምባሳደር ምስጋኑ ጠይቀዋል። 


 

የአየርላንድ የዓለም አቀፍ ልማትና ዳያስፖራ ሚኒስትር ዴኤታ ሲያን ፊሊሚንግ በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አየርላንዷ መዲና ዱብሊን ሳምንታዊ በረራ መጀመሩን ገልጸዋል።

አየርላንዳውያን ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ላመድረግ እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስፋት መስማማታቸውን አድንቀው በኢንቨስትመንት ዘርፉም ማጠናከር እንደሚገባቸው አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉደይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም