በፖሊስ አመራሮችና አባላት እየለማ የሚገኝ ከ70 ሄክታር በላይ የጤፍ ማሳ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
በፖሊስ አመራሮችና አባላት እየለማ የሚገኝ ከ70 ሄክታር በላይ የጤፍ ማሳ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19/2016(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል በፀጥታና ህግ ዋና መምሪያ በአቬዬሽን ፖሊስ መምሪያ ስራ ላይ የተሰማሩ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ያለሙት ከ70 ሄክታር በላይ የጤፍ ማሳ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል።
አመራርና አባላቱ ከተሰማሩበት የደህንነት ጥበቃ ስራቸው ጎን ለጎን የከተማ ግብርና ልማትን ከግብ ለማድረስ አርአያነት ያለው ተግባር ማከናወን መቻላቸው በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ለአቬዬሽን ፖሊስ መምሪያ የቢሮ አገልግሎት መስጫ የሚሆን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ያስገነባውን የሰራዊት ቢሮም ተመርቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የፌደራል ፖሊስ ሠራዊት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የእርሻ ስራዎች ላይ እየተሰማራ የገቢ ምንጩን እያጠናከረ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያማላክታል።