ቀጥታ፡

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጽጋበ ክበበው የሹመት ደብዳቤያቸውን በጄኔቫ ለሚገኙ የተመድ ተቋማት አስረከቡ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2016 (ኢዜአ)፦በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጽጋበ ክበበው የሹመት ደብዳቤያቸውን በሲውዘርላንድ ጄኔቫ ለሚገኙ የተለያዩ የተመድ ተቋማት አቅርበዋል።

አምባሳደሩ በጄኔቫ የተመድ የአፍሪካ ልዩ አማካሪ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ፋቱ ሀዲያራ፣የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትና የተመድ አቶሚክ አጀንሲ ተወካዮች የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።


 

በተጨማሪም በተመድ የዕጽና ወንጀል መከላከል ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጋዳ ዋሌ፣የተመድ የተቀናጀ የኒውክለር ቦንብ የሙከራ እገዳ ስምምነት ተቋም ዋና ጸሐፊ ሮበርት ፈሎይድ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።


 

አምባሳደሩ በኦስትሪያ ቬይናም የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፕሮቶኮል ማክሲሚሊያን ሄኒግ ማስረከባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጽ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም