የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከናይጄርያ ጋር ላለበት የመልስ ጨዋታ ወደ ናይጄሪያ አቀና - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከናይጄርያ ጋር ላለበት የመልስ ጨዋታ ወደ ናይጄሪያ አቀና
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 18/2016 (ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከናይጄርያ አቻው ጋር ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ወደ ናይጀሪያ አቅንቷል።
ብሔራዊ ቡድኑ ጥቅምት 20 ቀን 2016 ከናይጄርያ አቻው ጋር ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ዛሬ ወደ ናይጀሪያ መጓዙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ብሔራዊ ቡድኑ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በትላንተናው ዕለት የመጨረሻ የሀገር ቤት ልምምዱን በመስራት ዛሬ ወደ ናይጄሪያ ማቅናታቸው ተገልጿል።