ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ተከናውኗል

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 17/2016 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ባለፉት 3 ወራት ብቻ ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር መከናወኑ ተገለጸ።

በትናንትናው ዕለት የጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 (2023/24) በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


 

በጉባኤው ባለፉት ሶስት ወራት አበረታች የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሥራ አፈፃፀም መመዝገቡ ተመላክቷል።

በባንኩ ዲጂታል አማራጮች በተከናወኑ ከ245 ሚሊዮን በላይ የገንዘብ ዝውውሮች ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን በላይ የሆነ የብር መጠን መንቀሳቀሱን ከባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም