ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቶ በቀለ ሙለታ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀድሞ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ፣ ፋና ብሮድከስቲንግ ኮርፖሬት እና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ በነበሩት አቶ በቀለ ሙለታ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑረው ሲሉም በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም