ቀጥታ፡

116ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 15/2016 (ኢዜአ)፦ "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የፀና የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ሀሳብ 116ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በመስቀል አደባባይ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።


 

በበአሉ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣የኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የተለያዩ ሀገራት ኤታማዦር ሹሞችና ፣ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ ወታደራዊ አታሼዎች፣ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የሠራዊቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።


 

በዝግጅቱ የሠራዊቱን ታሪክ፣ ተጋድሎና ለመላው አፍሪካ ያበረከተውን ተምሳሌታዊ ገድል የሚያሳዩ መርሐ-ግብሮች እየቀረቡ ነው።

መከላከያ ሠራዊቱ አሁን የደረሰበትን አስተማማኝ ቁመና የሚያሳዩ ትርኢቶች እየቀረቡም ይገኛሉ።


 

ሠራዊቱ ለኢትዮጵያ ሉኣላዊነት የከፈለውን ዋጋ እና ታሪካዊ ጀግንነቱን የሚያወሱ ሁነቶችም ናቸው እየታዩ የሚገኙት ።

116ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የፀና የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ሀሳብ በመላ ሀገሪቱ የሠራዊቱን ጀግንነት በሚያወሱ ሁነቶች እየተከበረ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም