ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጀግንነቱና ሰላም አስከባሪነቱ ከሀገር የተሻገረ ታላቅ ክብር ስምና ዝና ያለው ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 13/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጀግንነቱና ሰላም አስከባሪነቱ ከሀገር የተሻገረ ታላቅ ክብር፣ ስምና ዝና ያለው መሆኑ ተገለጸ።

116ኛው የሠራዊት ቀን " በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የፀና የድል ሠራዊት " በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የፊታችን ሀሙስ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።

እለቱን በማስመለከት በተለያዩ አካባቢዎች በመከበር ላይ ሲሆን በዛሬው እለትም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።

በሁነቱ ላይ የተገኙት የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዴል ጄነራል ጡምሲዶ ፊታሞ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጀግንነቱ፣ ሀገር ወዳድነቱና ሰላም አስባሪነቱ የላቀ ክብር ስምና ዝና ያለው ነው ብለዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በተለይም በሰላም አስከባሪነቱ ከሀገር የተሻገረ ታላቅ ክብር፣ ስምና ዝና ያለው መሆኑንም ጠቅስዋል።


 

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላጫ ጋሩማ፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጀግንነቱ፣ በሰላም አስከባሪነቱና በህዝብ አለኝታነቱ እውቅና፣ ክብርና ሙገሳ ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የዞኑ የስራ ሃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም