ቀጥታ፡

3ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በካይሮ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 12/2016 (ኢዜአ)፦ ሶስተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በካይሮ ተጀምሯል።

ድርድሩም ባልተፈቱ የቴክኒካል እና የህግ ማእቀፍ ጉዳዮች የተሻለ ውጤት ላይ ለመድረስ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል።


 

ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሰራ የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልዑካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም