የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያስገነባቸው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመርቀው ሥራ ጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያስገነባቸው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመርቀው ሥራ ጀመሩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር ኃይል ያስገነባቸው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመርቀው ሥራ ጀመሩ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሠራዊት ቀንን በዛሬው እለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል።
በክብረ በዓሉ ላይ የአየር ኃይል መሠረተ ልማቶችና የሰው ሃብትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
ፕሮጀክቶቹን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፤ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ከተመረቁት መሠረተ ልማቶች መካከል የአየር ኃይል አቪየሽን አካዳሚ ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችና ቤተ ሙከራ፣ የአቪየሽን የጥገና ወርክ ሾፕ፣ የአየር ኃይል ቴክኒሺያን ማረፊያ ቤቶች ይገኙበታል።
የዘንድሮው 116 ኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ሃሳብ በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ አመራርና አባላት በዛሬው እለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።