ቀጥታ፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2016(ኢዜአ)፦ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው።

116ኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን "በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ደረጃ እየተከበረ ነው።


 

በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ እና ሌሎች የአየር ኃይሉ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ህልውና ለዘመናት ተጠብቆ የቀጠለው ጀግኖቿ በከፈሉት መስዋዕትነት በመሆኑ አሁንም በፈተናዎች ሁሉ በጽናትና አይበገሬነት የሚሻገር የድል ሠራዊት መገንባቱ ተመላክቷል።


 

የሀገር መከላከያ ሠራዊት በዘመናዊ ደረጃ በተቋም የተመሠረተበትን ጥቅምት 15 ቀን 1900 መሠረት በማድረግ የሠራዊት ቀን በመጪው ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም