ቀጥታ፡

የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የኢትዮጵያ የሰራዊት ቀንን እያከበረ ነው

ጋምቤላ፤ ጥቅምት 11/2016(ኢዜአ)፦ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የኢትዮጵያ የሰራዊት ቀንን በጋምቤላ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ በመከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ መኮንኖችና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።


 

በዓሉ የፓናል ውይይትን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ነው እየተከበረ ያለው።

ዕለቱ እየታሰበ ያለው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሰራዊቱ እየከፈለ የመጣውን መስዋዕትነት ለመዘከር መሆኑም በዚሁ ወቅት ተጠቅሷል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም