ቀጥታ፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2016(ኢዜአ)፡- የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቢሾፍቱ የሚገኘውን የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል መርቀው ከፈቱ። 

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የተገነባው ይኸው ማዕከል የመማሪያ ክፍሎች፣ ቢሮዎች፣ ሆስፒታልና ካፍቴሪያ በውስጡ አካቷል ።


 

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ መምሪያው የሰራዊቱ የግዳጅ አፈጻጸሞ እንዲያድግ ውጤታማ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።   

በርካታ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ውጤታማ የመሃንዲስ ድጋፍን እያረጋገጠ ይገኛልም ነው ያሉት።   


 

በተለያዩ አካባቢዎች ሆስፒታሎች፣ ካምፖችንና የሰራዊቱ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑንም ተናግረዋል። 

በዚሁ ዓመትም ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት መታቀዱንም ገልጸዋል።  

በመርኃ ግብሩ በዛሬው ዕለት የተመረቁት የመረጃ ማዕከልና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል። 

በመርኃ ግብሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሠራዊቱ መኮንኖች ተገኝተዋል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም