ቀጥታ፡

የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 8/2016(ኢዜአ)፦የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መዋዕለ-ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።

የኢትዮጵያና የቻይና ኢንቨስትመንት ፎረም በቻይና  የኢትዮጵያ ኤምባሲና በተባባሪ የቻይና ኩባንያዎች አዘጋጅነት በቻይናዋ ሻንሀይ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።

በኢንቨስትመንት ፎረሙ ላይ ከ300 በላይ የቻይና ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ አህመድ ሺዴ፣የማዕድን ሚኒስትሩ ሃብታሙ ተገኝ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅ የኢንቨስትመንት አቅምና ምቹ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።


 

የፎረሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስራ ሃላፊዎቹ እንዲመለሱላቸው የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች ማቅረባቸውንና በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት መስራት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም