ቀጥታ፡

የፕሪሚየር ሊጉ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ መድን ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ መድን በመጀመሪያ ሁለት የሊጉ ጨዋታዎች በአንዱ ድል ሲቀናው አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል።

ተጋጣሚው ወላይታ ድቻ እስካሁን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ሲያሸንፍ በአንዱ ደግሞ ሽንፈት ገጥሞታል።

በሌላኛው የሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ሁለቱም ክለቦች በመጀመሪያ ሁለት ጨዋታቸው ድል አልቀናቸውም።

ሲዳማ ቡና በሁለቱ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ሲያገኝ፤ ተጋጣሚው ፋሲል ከነማ ሁለት ነጥብ ማግኘት ችሏል።

የፕሪሚየር ሊጉ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገም ቀጥሎ ሲውል ሀዲያ ሆሳዕና ከወልቂጤ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት እንዲሁም የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሻሸመኔ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት የሚጫወቱ ይሆናል።

የሶስተኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች እስከ እሁድ ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም