ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2016 (ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የኢትዮጵያ፣ የእስራኤል እና የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ውይይታቸው ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችል ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረጉም ተገልጿል።