ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና ታላቁ የህዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና ታላቁ የህዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 06/2016 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን በቻይና ታላቁ የህዝብ አዳራሽ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በሁለትዮሽ ውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳንት ሺ በኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንኳን ደስ ያለዎ ብለዋቸዋል።
የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት (All Weather Strategic Cooperation Partnership) ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል።
ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል ማረጋገጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ኢንቬስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ያነሱ ሲሆን በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች-በግብርና ማኑፋክቸሪንግ አይሲቲ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ተጨማሪ ኢንቬስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ አቅርበዋል።