ቀጥታ፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2016(ኢዜአ)፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች 16ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች አክብረዋል፡፡

በዓሉ የተከበረው "የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው" በሚል መሪ ቃል ነው።

የአገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች በሀገሪቱ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጉልህ አስተዋጽዖ በማበርከት የሉዓላዊነትና የአንድነት ምልክት የሆነችው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብላ እንድትውለበለብ ዛሬም መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የውስጥና የውጭ ጠላቶች ዛሬም እንደትናንቱ የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ፣ ክብሯን ለማዋረድና ሰንደቅ ዓላማዋን ዝቅ ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ክብሯ የተጠበቀ፤ ድንበሯ የታፈረና በወጀብ ውስጥ ፀንታ የምትቆም ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ግንባር ቀደም በመሆን ስምሪታቸውን እንደሚወጡ ቃል መግባታቸውን አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ የላከው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም