ቀጥታ፡

ሠንደቅ ዓላማችን የማንነታችን መገለጫና የብልፅግናችን ማረጋገጫ ዓርማችን ነው- ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ

ሰመራ ፤ ጥቅምት 05/2016(ኢዜአ)፡- ሠንደቅ ዓላማችን፤የማንነታችን መገለጫ፣የብልፅግናችን ማረጋገጫና  የነፃነታችን ማሣያ ዓርማችን  ነው" ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተናገሩ።

የ16ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን "የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው"  በሚል መሪ ሐሳብ በሠመራ ከተማ  ዛሬ ተከብሯል።


 

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ፤  የሠንደቅ ዓላማ ቀን  አንድነታችንን የምናረጋግጥበት  ነው ሲሉ ገልጸዋል።

"እንኳን እኛ ግመሎቻችን የኢትዮጵያን ሠንደቅ ያውቋታል"በማለት  የሱልጣን አሊሚራህ ሐንፍሬን መልዕክት ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድር አወል፣ የአፋር ሕዝብ ዛሬም ለሀገሩና ለሠንደቅ ዓላማው ቀናዒ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አሲያ ከማል በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ኅብረብሄራዊ አንድነታችንን ያረጋገጥንበት መገለጫችን ነው ብለዋል።

ሀገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር የልማት ሥራዎችን ማከናወንና ሰላምን ማስጠበቅ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል።


 

የአፋር ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋጡማ አደን፤ በጀግኖች አባቶች መስዋዕትነት ተጠብቆና ተከብሮ የኖረውን ሠንደቅ ዓላማ ትውልዱም እንዲያስጠብቀው  መልዕክት አስተላልፈዋል።

የ16ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞችም መከበሩን ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም