ሰንደቅ ዓላማችን የአብሮነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የነፃነታችን ህያው ምልክት ነው - ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው - ኢዜአ አማርኛ
ሰንደቅ ዓላማችን የአብሮነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የነፃነታችን ህያው ምልክት ነው - ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው
ጥቅምት 5/2016 (ኢዜአ) ፡- ሰንደቅ ዓላማችን የአብሮነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የነፃነታችን ህያው ምልክት ነው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።
16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ተከብሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት አቶ እንዳሻው ጣሰው፥ ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችንና የሕብረ-ብሔራዊነታችን መገለጫ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም የአብሮነት፣ የሉዓላዊነትና የነፃነት ህያው ምልክት መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል በመላ ሃገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል።