የሉዓላዊነትና የነፃነታችን ዓርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን-ኮሚሸነር ደመላሽ ገብረሚካኤል - ኢዜአ አማርኛ
የሉዓላዊነትና የነፃነታችን ዓርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን-ኮሚሸነር ደመላሽ ገብረሚካኤል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2016 (ኢዜአ)፦ የሉዓላዊነትና የነፃነታችን ዓርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሸነርና የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት የወቅቱ ፕሬዝዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡
16ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረብሔራዊ አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው " በሚል መሪ ሃሳብ በፌዴራል ፖሊስ ቅጥር ግቢ ተከብሯል።
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል እና የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት የወቅቱ ፕሬዝዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤል ጨምሮ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራልና የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት የወቅቱ ፕሬዝዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ጊዜ፤ አባቶቻችን ያስረከቡንን የሉዓላዊነት ምልክት ፣ የነፃነታችን ዓርማ እና የክብራችን መገለጫ የሆነውን ሰንደቅዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን ብለዋል።
በመላው ሀገሪቱ ያሉ የፖሊስ አባላት ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ዘወትር ዘብ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
በዓሉ በፓናል ውይይትና ሌሎች የሰንደቅ ዓላማን ክብር ከፍ በሚያደርጉ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪው ሰኞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 ተደንግጎ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡