ቀጥታ፡

16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2016 (ኢዜአ)፦16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው።

"የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው" የሰንደቅ ዓላማ ቀን መሪ ቃል ነው የዘንድሮው የሰንደቅዓላማ ቀን እየተከበረ የሚገኘው።

ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በዋጀ መልኩ ከሰንደቅ ዓላማ መርሆች ጋር ተገናዝቦና ሀገራዊ ሪፎርሙን በሚያስቀጥሉ ውይይቶች ታጅቦ በመላ ሀገሪቷ እየተከበረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በዛሬው ዕለት በዓሉ፤ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎች እና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4 ሰዓት ተኩል ላይ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።

የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪው ሰኞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 ተደንግጎ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም