የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2016 (ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ያስገነባቸው ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች ዛሬ ተመረቁ።
በዛሬው ዕለት የተመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።
የመንገድ ፕሮጀክቶቹ የቦሌ ሚካኤል ተሻጋሪ ድልድይን ጨምሮ ከአራራት ሆቴል - ኮተቤ ኮሌጅ፣ ከኮተቤ ኮሌጅ - ካራ (ሎት2)፣ ከቄራ ከብት በረት - ጎፋ መብራት ኃይል፣ ከቀጨኔ - ቁስቋም፣ ከየካ አማኑኤል ሆስፒታል - ኮተቤ እንዲሁም ሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ አያት 2 ኮንዶሚኒየም፣ አያት መሪ ሳይት 4 ናቸው።
ዛሬ የተመረቁት መንገድ ፕሮጀክቶች በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በማቃለል የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያስችላል ተብሏል።
በምረቃ መርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ ጨምሮ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።