የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 01/2016(ኢዜአ)፦ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሲጀመር ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ይጫወታሉ።
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያ ጨዋታቸው ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፋቸው ይታወቃል።
ሌላኛው የሊጉ ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሀዲያ ሆሳዕናን ያገናኛል።
አዲስ አዳጊው ንግድ ባንክ በመጀመሪያ ጨዋታው አቻ ሲወጣ ተጋጣሚው ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ ሽንፈት ገጥሞታል።
የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገም ቀጥሎ ሲውል ሀምበሪቾ ዱራሜ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 9 ሰዓት፤ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ከምሽቱ 12 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ ጥቅምት 4/2016 ይቆያሉ።