የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለጻ እያደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለጻ እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለጻ እያደረገ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፤ በዚሁ ጊዜ ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለምክክሩ መጀመር መሰረታዊና ወሳኝ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁመዋል።
በዚህም አገራዊ ምክክሩ አካታችና አሳታፊ እንዲሆን ለማስቻል ከፌዴራል እስከ ክልሎች፤ ከክልሎች አስከ ዞኖችና ወረዳዎች በመድረስ ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ እንደቆየ አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅትም የተሳታፊዎች ልየታ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
አለም ዓቀፉ ማኅበረሰብም እስካሁን ለኮሚሽኑ እያደረገ ላለው ድጋፍ እውቅና በመስጠት በቀጣይም ይህ አገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።