ቀጥታ፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከቶኒ ብሌይር ኢኒስቲትዩት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2016(ኢዜአ)፦የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከቶኒ ብሌይር ኢንስቲትዩት የስራ ሃላፊዎች ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የቶኒ ብሊዬር ኢንስቲትዩት ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር የሚሰራቸዉ የትብብር ስራዎች ዉጤት ያመጡና የእዉነተኛ ትብብር ማሳያዎች ናቸው።

ይህንን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ነመራ ገበዬሁ በበኩላቸዉ የቶኒ ብሊዬር ኢንስቲትዩት በተለይ በክትትልና ግምገማ ዘርፍ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ስራ ጠንካራ የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር የተያያዙ መመሪያዎችና ሌሎች አጋዥ ሰነዶችን በጋራ እየተዘጋጁ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

የፐብሊክ ኢንቨስትመንት አስተዳደርን በተመለከተም በዩናይትድ ኪንግደም የዳበረ ልምድ መኖሩን በመግለጽ ኢንስቲትዩቱ ኩባንያዎችን የማስተሳሰርና ልምድ የሚገኝበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

የቶኒ ብሊዬር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወይዘሮ ማለዳ ብስራት በበኩላቸዉ ኢኒስቲትዩቱ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር የጀመራቸውን የትብብር ስራዎች እንደሚያጠናክር ማረጋገጣቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለ28ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብርት ለውጥ ጉባዔ እየተደረገ ያለው ዝግጅትም በመድረኩ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም