ቀጥታ፡

ከ2015 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ያለፉት 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ ናቸው-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2016(ኢዜአ)፦ ከ2015 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ያለፉት 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የዘንድሮው ፈተና በጥቅሉ በ2014 ዓመት ከነበረው በጣም  ለውጥ የታየበትና ከኩረጃና ሌብነት የጸዳ እንደነበር ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በ2015 ከተፈተኑ ተማሪዎች ውስጥ ያለፉት 50 በመቶ ውጤት በማምጣት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚያስገባ ውጤት ያመጡት 27 ሺህ 267 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህም ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ ያመጡት 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ከ700 በማምጣት መመዝገቡን ገልጸው፤ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ከ600 ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ከተፈጥር ሳይንስ ተፈታኞች ውጥስ 205 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 15 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ነው ያነሱት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም