የኢሬቻ በዓል ብዝሃ ማንነቶችን በጋራ የሚያስተሳስር የአብሮነት መገለጫ ነው-የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ ሳሙኤል ፎላ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2016(ኢዜአ)፦ የኢሬቻ በዓል ብዝሃ ማንነቶችን በጋራ የሚያስተሳስር የአብሮነት መገለጫ መሆኑን በሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የታደሙት የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ ሳሙኤል ፎላ ተናገሩ።

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ የአንድነት እና የወንድማማችነት አርማ" በሚል መሪ ሀሳብ  ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በመጡ ታዳሚዎች ደምቆ ተከብሯል፡፡

በበዓሉ የታደሙት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ፎላ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በዓሉ ወንድማማችነትና አብሮነትን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መስፈን ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በበዓሉ ላይ መታደማቸው የበዓሉን አከባበር ልዩ ገጽታ እንዳላበሰውም ጠቁመዋል፡፡

ይህም ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም