የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2016 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋሉ።
ሻሸመኔ ከተማ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት እንዲሁም ሀምበሪቾ ዱራሜ ከድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ይጫወታሉ።
ሀምበሪቾ ዱራሜ እና ሻሸመኔ ከተማ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ክለቦች ናቸው።
ነገ የሊጉ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ሃዋሳ ከተማ ከፋሲል ከነማ ከቀኑ 9 ሰዓት፤ ሀዲያ ሆሳዕና ከመቻል ከምሽቱ 12 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መስከረም 20/2016 መጀመሩ ይታወቃል።
በመክፈቻው ቀን በተደረጉ ጨዋታዎች የአዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ-ግብር እስከ መስከረም 27/2016 የሚቆይ ይሆናል።