በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ከ17ተኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ ካሳዬ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ ከ17ተኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ ካሳዬ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24/2016 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሀዲ ከ17ተኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ ካሳዬ ጋር ተወያዩ።
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል በዩናሚስ ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ሱዳን ህዝብና መንግስት ጥሩ ስም ያላቸው በመሆኑ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
ሰላም አስከባሪው እስከ አሁን እያደረገ ስላለው የሠላም አስተዋፅኦ ምስጋና ያቀረቡት አምባሳደሩ ለቀጣይ በሚያስፈልገው ነገሮች ሁሉ ኤምባሲው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የ17ተኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሞገስ ካሳዬ በበኩላቸው የሰላም አስከባሪ አባላቱ አስቸጋሪው ቦታና አየር ፀባይ ሳይበግራቸው ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።