የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች አስመረቀ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2016(ኢዜአ)፦ በኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለስድስት ወራት በመሰረታዊ ውትድርና ሙያ ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች ዛሬ አስመረቀ።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ጨምሮ ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርኃ ግብሩ በ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት በበረራና ቴክኒሻን የሙያ ዘርፎች ትምህርትና ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ሠልጣኞች የትከሻ ምልክት (ፍላግ) የማልበስ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።