ቀጥታ፡

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮዮጵያ 650 ሚሊዮን ዩሮ አመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ መርሃ-ግብር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2016 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮዮጵያ 650 ሚሊዮን ዩሮ አመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ መርሃ-ግብር ይፋ አድርጓል።

የድጋፍ ማዕቀፉን የአውሮፓ ህብረት የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ፈርመዋል።

መርሃ-ግብሩ ላይ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች ታድመዋል።

ኮሚሽነር ጁታ በዚሁ ወቅት ድጋፉ በኢትዮጵያ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ማግስት ይፋ መደረጉ የአውሮፖ ህብረት ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ያሳየበት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ይህ ድጋፍ በዋናነት በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ ውስጥ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ድጋፉ ለሁለተኛው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምና ለዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ትግበራ የሚውል ይሆናል ብለዋል።

እንዲሁም ድጋፉ ለአረንጓዴ ልማት ፣ለአየር ንብረት ለውጥ ፣ ግብርና ፣አካባቢ ጥበቃና ታዳሽ ኃይል ልማት፣ ለሰው ኃይል ልማት እንዲሁም አስተዳደር፣ ሰላም ግንባታና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚውል ይሆናል ነው ያሉት።

ኮሚሽነር ጁታ በዛሬ ውሎዋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ :ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር መምከራቸው ታውቋል።

ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን በኢትዮጵያ ይፉዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም