አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1 ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸነፈች 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016 (ኢዜአ)፦  በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸንፋለች። 

ርቀቱን አትሌት ድርቤ ወልተጂ 4 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን ስትጨርስ ፍሬወይኒ ኃይሉ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ቀደም ብለው በተደረጉ ውድድሮች በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ሀጐስ ገ/ሕይወት 12 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት 1ኛ ሲወጣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ 13 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

በተመሳሳይ አትሌት እጅጋየሁ በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ሆና ማጠናቀቅ ማጠናቀቅ መቻሏም እንዲሁ።

በላቲቪያ ሪጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሚደረገው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው 13 አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በሻምፒዮናው ከ57 አገራት የተወጣጡ 347 አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን 1 ማይል፣ 5 ኪሎ ሜትር እና የግማሽ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች ውድድር የሚካሄድባቸው ርቀቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም