በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀናቸው - ኢዜአ አማርኛ
በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2016 (ኢዜአ)፡- ዛሬ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች 1ኛና 2ኛ በመውጣት ድል ቀንቷቸዋል።
በውድድሩም አትሌት ሀጐስ ገ/ሕይወት 12 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት 1ኛ ሲወጣ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ 13 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በተመሳሳይ አትሌት እጅጋየሁ በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች።
በዚሁ እርቀት የተሳተፈችው አትሌት መዲና ኢሳ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡
ኬንያዊቷ አትሌተ ቢያትሬስ ቼቤት ውድድሩን በአንደኛነት አሸንፋለች።