የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20 /2016(ኢዜአ)፡- የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።

በ16 ክለቦች መካከል የሚከናወነው የወንዶች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ መካሄዱን የሚቀጥል ይሆናል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አዳማ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ከቀኑ 9 ሰዓት የሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ያደርጋሉ።

በመቀጠልም ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ መስከረም 27 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄዱ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር እስከ የካቲት 10ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

የሊጉ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአዳማና ድሬዳዋ ከተሞች እንደሚደረግም ታውቋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሻሸመኔ ከተማና ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ክለቦች መሆናቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም