ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል 

202

አዲስ አበባ፤ መስከረም 18/2016 (ኢዜአ)፦ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2023/24 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከግብጹ አል አህሊ ጋር ዛሬ ያከናውናል።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ 75 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው በካይሮ  ኢንተርናሽናል ስታዲየም  ከምሽቱ 1 ሰዓት ይካሄዳል።
 

ክለቦቹ መስከረም 13/2016 በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አል አህሊ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባት ተጋጣሚውን ከሶስት ግብ ልዩነት በላይ ማሸነፍ ይኖርበታል።

ማሊያዊው ቡቡ ታሪ የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
አል አህሊ የባለፈው ውድድር ዓመት የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም