በ49ኛው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ላሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ አቀባበል ተደረገላት

አዲስ አበባ ፤መስከረም 18/2016(ኢዜአ)፦በ49ኛው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ላሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደረገላት።

አትሌቷ ከአሰልጣኟ ጋር ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ስተገባ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተገኝተው አቀባበል አድርገዋል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይም የአበባ ጉንጉን ተበርክቷል።

በ49ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2:11:53 ውድድሩን በመጨረስ የአለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን መስበሯ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም