በከተማችን ባሉ የምገባ ማዕከላት ከ35 ሺህ በላይ ወገኖቻችን አገልግሎት እያገኙ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባሉ 20 የምገባ ማዕከላት ከ35 ሺህ በላይ ወገኖች አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ 20ኛውን የአዲስ አበባ ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን ዛሬ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡


 

በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ የምገባ ማዕከሉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቀጨኔ መድሃኒያለም በሚባለው አካባቢ መገንባቱን ጠቅሰዋል።

ማዕከሉ ከ500 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው አቅመደካማ ነዋሪዎች በቀን አንድ ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ የሚያቀርብ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡


 

የምገባ ማዕከሉን በ47 ሚሊየን ብር ለገነባው ቶኩማ ስታር ቢዝነስ ግሩፕ እንዲሁም ተገልጋዮቹን በቋሚነት ለመመገብ ማዕከሉን ለተረከበው የብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከንቲባዋ አጠቃላይ በከተማዋ ባሉ 20 የምገባ ማዕከላት ከ35 ሺህ በላይ ወገኖች አገልግሎት እያገኙ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም