የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንጉዊ በረራ ሊጀምር ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንጉዊ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 17/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ርዕሰ መዲና ባንጉዊ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
ከሕዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ባንጉዊ በሳምንት ሶስት ጊዜ የሚበር መሆኑን አየር መንገዱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ ጠቁሟል።
ለአየር መንገዱ ባንጉዊ 64ኛ የአፍሪካ መዳረሻ እንዲሁም በዓለም 135ኛ መደረሻ ትሆናለች።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይም ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎችን የማስፋት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።