ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ 20ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ 20ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 17/2016 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ 20ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከሉን የመረቁት።
የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተገነቡ የምገባ ማዕከላት በቀን ከ35 ሺህ በላይ ዜጎች እየተመገቡ መሆኑም ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በመዲናዋ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነባውን 20ኛውን የምገባ ማዕከል መርቀው በይፋ ስራ ያስጀመሩ ሲሆን በወቅቱም ለአቅመ ደካሞች ማእድ አጋርተዋል።