በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነዉ

68

ጋምቤላ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ከተማና አካባቢው የመስቀል ደመራ በዓል ሐይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በሊቃውንት ያሬዳዊ ሽብሸባና በተለያዩ ሐይማኖታዊ ስርዓቶች ነዉ እየተከበረ ያለው።

የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ትውፊቱ ባለፈ የቱሪስት መስህብ በመሆን ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አወንታዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በዓሉ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /በዩኒስኮ/ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑ ይታወሳል።

በዓሉ የጋምቤላ ፣ የአሶሳ ፣ የቄሌም ወለጋና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ተወካይ ፣ሊቃዉንት አባቶችና የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በጋምቤላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም