የመስቀል ደመራ በዓል በሀዋሳ እየተከበረ ነው

ሀዋሳ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል ዋዜማ ደመራ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

ከሀዋሳ ከተማ የሃይማኖት አባቶች የዕምነቱ ተከታዮችና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የውጭና የሃገር ውስጥ ጎብኚዎች በተገኙበት የደመራ በዓል እየተከበረ ሲሆን ከመስቀል አደባባይ ባሻገር ምእመናንም በየቤተክርስቲያናቱና በቤታቸው ደመራ በመለኮስ ያከብሩታል።

በሀዋሳው የደመራ በዓል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ጥንግ ድርብ የለበሱ ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተለያዩ ዝማሬዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

በደመራው መርሀ-ግብር ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሲዳማ ሃገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቢ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ እና የአብያተ ክርስቲያናት ካህናትና ምእመናን ተገኝተዋል።

የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪ ባሉት ባህላዊ ትዕይንቶቹ በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም