የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦ የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይ በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ  አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ  አብርሃም፣ የቅዱስ  ሲኖዶስ  ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና  አካባቢው ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ  ብፁዕ  አቡነ ጴጥሮስ፣ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል።


 

የደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከናወኑ ሲሆን በዓሉን የተመለከቱ ያሬዳዊ ዝማሬዎችም በመቅረብ ላይ ናቸው።

የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ነው።

በዓሉ እ.አ.አ በ2013 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም