የሀረሪ ክልል ለመስቀል ደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለመስቀል ደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

በመልዕክቱም ህዝበ ክርስትያኑ የደመራ በዓል አከባበር እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በማድረግ የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን እንዲያከብር ጥሪውን አቅርቧል።

ህዝበ ክርስትያኑን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጎልበት እንዲሁም በክልሉ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የልማት ተግባራት እንዲጠናከሩ ድጋፋን እንዲያጠናክር የክልሉ መንግስት ጠይቋል።

የክልሉ መንግስት በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራና ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ብሏል።

በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ተመኝቷል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም