የውጭ አገራት ጎብኚዎች በአገር ውስጥ የሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የቱሪዝም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦  የውጭ አገራት ጎብኚዎች በኢትዮጵያ የሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። 

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ልዩ ቦታ ከሚሰጣቸው ወራቶች ውስጥ የመስከረም ወር አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

የዘመን መለወጫ ዕንቁጣጣሽ፣ የመስቀል ደመራ፣ ያሆዴ መስቀላ፣ ዮ ማስቃላ፣ ጊፋታና እሬቻ በመስከረም ወር ብቻ የሚከበሩ በዓላት ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ የመስከረም ወር በርካታ የውጭ አገራት ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት ወር እንደሆነ ይታወቃል።

በዓላቱ አብሮነትን በማጠናከርና ሕዝብን በማቀራረብ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ሲሆን ጎብኚዎችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ይታወቃል።

ይህንን ወቅት ተከትሎ በዘርፉ ምን አይነት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ሲል ኢዜአ የቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ነጋሽን አነጋግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ሚኒስቴሩ የአገሪቱን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለጎብኚዎች በስፋት ሲያስተዋውቅ መቆየቱን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። 


 

በተጓዳኝም፤ የክልል ቱሪዝም ቢሮዎችም መሰል ሥራዎችን መከናወናቸውንም እንዲሁ። 

ጎን ለጎንም ለበዓላቶቹ ለሚመጡ የውጭ አገራት ጎብኚዎች የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅና ቆይታቸውን የሰመረ ለማድረግ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።


 

ጎብኝዎች ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን ከአቀባበል ጀምሮ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው አስፈላጊ መረጃዎችን የሚያሳውቅ የጎብኚዎች መረጃ ማዕከል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ተናግረዋል።

ከመሥተንግዶ ጋር በተያያዘ እክል እንዳይገጥማቸው ከሆቴሎችና ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።

  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም