የመውሊድና የመስቀል ደመራ በዓላትን ስናከብር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህላችንን ይበልጥ በማጠናከር መሆን አለበት- ርእሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፤መስከረም 16 /2016 (ኢዜአ)፡- የመውሊድና የመስቀል ደመራ በዓላትን ስናከብር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህላችንን ይበልጥ በማጠናከር መሆን አለበት ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን ለእስልምና እምነት ተከታዮችም እንኳን ለ1ሺ 498ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። 

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ''የመውሊድና የመስቀል ደመራ በዓላትን ስናከብር ከአጠገባችን ያሉትን አቅመ ደካሞች በማሰብ መሆን ይገባል'' ብለዋል።

በተለይም በሲዳማ ክልል የበዓሉ አክባሪዎች የተቸገሩትን በመርዳት፣ ያጡትን በመደገፍ፣ በመተሳሰብና ፍቅርን በመግለፅ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙስሊሙም ይሁን ክርስትያኑ በዓላቱን ሲያከብር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህልን ይበልጥ በሚያጠናክር መልኩ መሆን አለበትም ነው ያሉት።

''የበዓላቱን ዕሴቶች ከፍ በማድረግ አንድነታችንንና ህብረታችንን በሚያጎሉ ክንውኖች ማክበር ይገባልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም