በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን ከማገዝ ባሻገር የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ ሊሆን ይገባል- ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ - ኢዜአ አማርኛ
በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን ከማገዝ ባሻገር የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ ሊሆን ይገባል- ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦ በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን ከማገዝ ባሻገር የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።
1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጊድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን ከማገዝ ባሻገር የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ሰላም የሁሉም መሰረት ነው ያሉት ኃላፊዋ፤ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።